የእምነት ፅድቅ
ሮሜ 4
²⁰-²¹ ለእግዚአብሔርም ክብር እየሰጠ፥ የሰጠውንም ተስፋ ደግሞ ሊፈጽም እንዲችል አጥብቆ እየተረዳ፥ በእምነት በረታ እንጂ በአለማመን ምክንያት በእግዚአብሔር ተስፋ ቃል አልተጠራጠረም።
²² ስለዚህ ደግሞ ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት።
²³ ነገር ግን፦ ተቈጠረለት የሚለው ቃል ስለ እርሱ ብቻ የተጻፈ አይደለም፥ ስለ እኛም ነው እንጂ፤
²⁴-²⁵ ስለ በደላችን አልፎ የተሰጠውን እኛን ስለ ማጽደቅም የተነሣውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሣው ለምናምን ለእኛ ይቈጠርልን ዘንድ አለው።
እንዴት ድንቅ ቃል ነው። አብርሃም እግዚአብሔር የተናገረውን እንደሚፈጽም በማመን በእምነት አልጠራጠረም አጥብቆ ተረድቷል ስለዚህም እግዚአብሔር አብርሃምም ጽድቅ ሆኖ ተቆጥሮለታል። የእኛም እንደዚሁ ነው። እኛን ለመጽደቅ በክርስቶስ የመስቀል ሥራ ላይ የማያወላውል እምነት ሊኖረን ይገባል ምክንያቱም የእግዚአብሔር ኃይል ክርስቶስን ከሙታን አስነስቶ እኛን መዳን የሚገኝበትን ይህ ጽድቅ እንደተቆጠርን ያረጋግጥልናል።
እግዚአብሔር የታመነና የገባውን ቃል ለማድረግ የሚችል ነው። ሃሌ ሉያ!
ፀጋ ይብዛላችሁ 🥰🙏
ወንድማችሁ ይሳቅ

አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ