ጳውሎስ ለማስተማር ሲሞክር ጌታውን አልታዘዘም ነበር።

 እንዲህ ብለን እንጀምር ጳውሎስ ለማስተማር ሲሞክር ጌታውን አልታዘዘም ነበር


(ማቴዎስ 23: 8-10) እና በክርስቶስ ተልእኮ እና መንግሥት ላይ ከማንም በላይ ጉዳት አድርሷል ምክንያቱም ሁሉም "የሚባሉት የጳውሎስ መልዕክቶች እና የክርስቶስ የምድር  ትምህርት አንድ አይነት አይደሉም!!! ስለዚህም ችግሩ ያለው ከጳውሎስ ነው ወይስ ያልገባን መፅሀፉን አንባቢዎች ነን???



መልሴ፡-

  አብዛኞቹ “የሚባሉት” የክርስትና ሃይማኖቶች የመንግሥቱን ወንጌል (ትምህርት) ያስተምራሉ እና ጳውሎስን መልዕክቶች ችላ ይላሉ።  ሁሉም ሰባኪ የአራቱ ወንጌሎች ያስተምራል  እናም አልፎ አልፎ ካልሆነ ከጳውሎስ መልእክቶች ማስተማር ብዙ አይደፈርም ይህም በእውነቱ ዛሬ ለክርስቶስ አካል  ትምህርት ነውን ???

ኢየሱስ (እና 12ቱ) ሐዋርያት ያስተማሩት አራቱ ወንጌሎችና የመንግሥቱ ወንጌል መልእክት ለእስራኤል ትምህርት ነው።  እሱም ለአይሁዶች እና ምድራዊ መንግስት ዓላማ እና ርስታቸው በምድራዊው የሺህ ዓመት መንግሥት ውስጥ የተለየ ትንቢታዊ ትምህርት ነው።  ኢየሱስ በምድር የመጣው ለአይሁዶች ብቻ መሆኑን የሚያረጋግጡትን ቅዱሳት መጻህፍት አስተውሉ፡-

ማቴዎስ 15፡24 እርሱ ግን መልሶ፡— ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች በቀር አልተላክሁም አለ።

ማቴዎስ 10፡5-6 እነዚህን አሥራ ሁለቱን ኢየሱስ ላካቸውና አዘዛቸው፡— በአሕዛብ መንገድ አትሂዱ፥ ወደ ሳምራውያንም ከተማ አትግቡ፤ (6) ነገር ግን ወደ ጠፉት በጎች ሂዱ እንጂ። ይህመሰ  ለእስራኤል ማለት ነው ግልፅ ነው።

ሮሜ_15፡8 አሁንም ለአባቶች የተሰጠውን የተስፋ ቃል ያጸና ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እግዚአብሔር እውነት የመገረዝ አገልጋይ ነበረ እላለሁ።

እንግዲህ ጳውሎስ የአሕዛብን ሐዋርያ፣ የጌታን ትእዛዛት በማድመቅ የጻፈውን ሀሳብ ልብ በል።

ሮሜ 11፥13-14  “ለእናንተም ለአሕዛብ እናገራለሁ። እኔ የአሕዛብ ሐዋርያ በሆንሁ መጠን ሥጋዬ የሆኑትን አስቀንቼ ምናልባት ከእነርሱ አንዳንዱን አድን እንደሆነ አገልግሎቴን አከብራለሁ።”

1ኛ ቆሮ 14፡37 ማንም ራሱን ነቢይ ወይም መንፈሳዊ ነኝ ብሎ የሚመስለው ከሆነ እኔ የምጽፍልህ የጌታ ትእዛዝ እንደ ሆነ ይወቅ።

1ኛ ቆሮንቶስ 4:16 ስለዚህ እኔን የምትመስሉ ሁኑ ብዬ እለምናችኋለሁ።

1ኛ ቆሮ 11፡1 እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ።

1ኛ ጢሞቴዎስ 1፡16 ስለዚህ ነገር ግን የዘላለምን ሕይወት ለማግኘት በእርሱ ያምኑ ዘንድ ላላቸው ምሳሌ እንድሆን፥ ኢየሱስ ክርስቶስ በእኔ በመጀመሪያ ትዕግሥቱን ሁሉ ያሳይ ዘንድ ምሕረትን አገኘሁ።

የጳውሎስና መልዕክቶቹ ችግር አይደሉም በጳውሎስ የተጀመረ ከእርሱ የጀመረ አዲስ አገልግሎት፣ አዲስ ትምህርት፣ አዲስ ዘመን እና አዲስ ፍጥረትነት አለ ይህን መረዳት የመፅሀፍትን እንቆቅልሽ ይፈታልናል ።  የእሱ አስተምህሮ ብዙዎች ቤተክርስቲያናት ችላ የሚሉት  ግን መፅሀፍትን ለመረዳት መፍትሄ የሆነ ነው። ከፋፍሎ ካለማጥናት የተነሳ  በዚህ ምክንያት ነው ዛሬ ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ያለ ውዥንብር ውስጥ የምትገኘው ግራ የተጋባች እና እርስ በርሱ በሚጋጭ ትምህርት የመንግሥቱን አስተምህሮ ከፀጋው ትምህርት የምትቀላቅለው። ስለዚህ ለእኛ ያልተነገረን ወይም ለእኛ ያልተዘጋጀልን ትምህርት መከተል የለብንም።  ሰማይን እንጂ ምድርን አንወርስም በሞትና በትንሳኤው መልእክት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በጳውሎስ ብእር መሪነት የተሰጠን የራሱ ልዩ ትምህርት ያለው ፍጹም የተለየ ዘመን ውስጥ ነን።  የጸጋውን ትምህርት ከተረዳህ፣ የተመሰቃቀለውን ያጸዳል እና ግልጽነትን እና የሰማይን ሀገርነት  አላማ ለክርስቶስ አካል ያጠራል ያስረዳል  ያመጣል።

 ፀጋ ይብዛላችሁ 
ወንድማችሁ ይሳቅ

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ጸድቀናል (ታረቅን)

ኩነኔ የለብንም

እምነት መገኛው ቃሉ ነው