የእስራኤል እና የክርስቶስ አካል ልዮነት
የክርስቶስ አካል የሆነችው ቤተ ክርስቲያን ከአይሁድና ከአሕዛብ የተዋቀረች አዲስ ፍጥረት እንጂ አሥራ ሁለት ነገድ የላትም። ጀስቲን ጆንሰን እንደተየበው በ ይሳቅ አሰፋ የተተረጎመ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አሥራ ሁለት ነገዶች ሲናገር፣ ስለ አንድ አካል ቤተክርስቲያን አይናገርም ለያይቶ ነው ያስቀመጣቸው (ሮሜ 12፡5፣ ኤፌ 1፥22-23 እና 4፡4)። አሥራ ሁለት የእስራኤል ነገዶች የእስራኤል ብሔር የሆኑ አሥራ ሁለት ቤተሰብ ነገዶች ነበሩ። እነዚያ ነገዶች ከአሥራ ሁለቱ የያዕቆብ ልጆች የመጡ ናቸው -(ዘፍ 49፡28)። እስራኤል ሕጉን ሁሉ ለማድረግ በተስማሙ ጊዜ፣ ሙሴ ለመታሰቢያ የሚሆን አሥራ ሁለት ሀውልቶች ሠራ፤ ለእያንዳንዱ የእስራኤል ነገድ አንድ ም። “ሙሴም የእግዚአብሔርን ቃሎች ጻፈ ማለዳም ተነሣ፥ ከተራራውም በታች መሠዊያን፥ አሥራ ሁለትም ሐውልቶች ለአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ሠራ።” — ዘጸአት 24፥4 በአሮን ኤፉድ ውስጥ እንደ አሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ አሥራ ሁለት ድንጋዮች ነበሩ። “የዕንቈቹም ድንጋዮች እንደ እስራኤል ልጆች ስሞች አሥራ ሁለት ይሆናሉ፤ በየስማቸውም ማተሚያ እንደሚቀረጽ ይቀረጹ፤ ስለ አሥራ ሁለቱ ነገዶችም ይሁኑ።” — ዘጸአት 28፥21 መልካሙንም ዱቄት ወስደህ አሥራ ሁለት ኅብስት ጋግር በአንድ ኅብስት ውስጥ ከመስፈሪያው ከአሥር እጅ ሁለት እጅ ይሁን። እነዚህንም ስድስት ስድስቱን በሁለት ተርታ አድርገህ በእግዚአብሔር ፊት በጥሩ ገበታ ላይ አኑራቸው።ለእግዚአብሔርም ለእሳት ቍርባን በእንጀራው ላይ ለመታሰቢያ ይሆን ዘንድ በሁለቱ ተርታ ላይ ጥሩ ዕጣን አድርግ።በእግዚአብሔር ፊት ሁልጊዜ በሰንበት ቀን ሁሉ ...