ልጥፎች

ከኦክቶበር, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የእምነት ፅድቅ

ምስል
 ሮሜ 4 ²⁰-²¹ ለእግዚአብሔርም ክብር እየሰጠ፥ የሰጠውንም ተስፋ ደግሞ ሊፈጽም እንዲችል አጥብቆ እየተረዳ፥ በእምነት በረታ እንጂ በአለማመን ምክንያት በእግዚአብሔር ተስፋ ቃል አልተጠራጠረም። ²² ስለዚህ ደግሞ ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት። ²³ ነገር ግን፦ ተቈጠረለት የሚለው ቃል ስለ እርሱ ብቻ የተጻፈ አይደለም፥ ስለ እኛም ነው እንጂ፤ ²⁴-²⁵ ስለ በደላችን አልፎ የተሰጠውን እኛን ስለ ማጽደቅም የተነሣውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሣው ለምናምን ለእኛ ይቈጠርልን ዘንድ አለው። እንዴት ድንቅ ቃል ነው።  አብርሃም እግዚአብሔር የተናገረውን እንደሚፈጽም በማመን በእምነት አልጠራጠረም አጥብቆ ተረድቷል ስለዚህም እግዚአብሔር አብርሃምም ጽድቅ ሆኖ ተቆጥሮለታል።  የእኛም እንደዚሁ ነው።  እኛን ለመጽደቅ በክርስቶስ የመስቀል ሥራ ላይ የማያወላውል እምነት ሊኖረን ይገባል ምክንያቱም የእግዚአብሔር ኃይል ክርስቶስን ከሙታን አስነስቶ እኛን መዳን የሚገኝበትን ይህ ጽድቅ እንደተቆጠርን ያረጋግጥልናል። እግዚአብሔር የታመነና የገባውን ቃል ለማድረግ የሚችል ነው።  ሃሌ ሉያ! ፀጋ ይብዛላችሁ 🥰🙏 ወንድማችሁ ይሳቅ

በአእምሮህ ውስጥ ምን አለ?

ምስል
ይህ የእምነት እና የክርስትና_ሕይወት ቁልፍ ነው።  የእምነታችሁ እና የክርስቲያናዊ ኑሮዎ ዋና ነገር በአእምሮአችሁ ውስጥ ባለው ነገር ላይ የተመሰረተ ነው። በእግዚአብሔር ቃል በሚታደስ እና በመንፈሳዊ ጥበብ እ እወነት መርህ ላይ በተመሰረተ አእምሮ እየሰራችሁ ነው ወይንስ በአለማዊ እውቀት እና ከንቱነት ላይ በተመሠረተ አእምሮ እየሰራችሁ ነው? በትክክል ስለተከፋፈለው ቃል እውቀት ማግኘት የህይወት እና የመንፈሳዊ ጥንካሬ ዋና አካል ነው። እምነትን ይጨምራል፣ በረከትን ይመግባችኋል፣ በእግዚአብሔር መንፈስ ይሞላችኋል፣ ለጌታ እንደሚገባ እንድትመላለሱ ኃይል ይሰጣችኋል፣ ከጠላት ጋር የምትዋጋበት ትጥቅ ነው። የመንፈሳዊ እወነት እውቀት መጨመር ከሁሉም በላይ አስፈላጊው ነገር ነው ግን በብዙ ክርስቲያኖች ሕይወት ውስጥ በጣም ዝቅተኛ ዋጋ ያለው ተግባር ሆኗል። መጽሐፍ ቅዱስ ለአእምሮ የሚሰጠውን ግምትና በመንፈስና በእውነት መታደስ ያለውን አስፈላጊነት ይህ ነው የማይባል ጠሊቅ ነው ቃሉን እንያዝ ቃሉን በክርስቶስ ኢየሱስ አእምሮአችንን የሚያድስ ነው። ፀጋ ይብዛላችሁ 🥰🔥 ወንድማችሁ ይሳቅ