የእስራኤል እና የክርስቶስ አካል ልዮነት

 የክርስቶስ አካል የሆነችው ቤተ ክርስቲያን ከአይሁድና ከአሕዛብ የተዋቀረች አዲስ ፍጥረት እንጂ አሥራ ሁለት ነገድ የላትም።

  ጀስቲን ጆንሰን እንደተየበው በ ይሳቅ አሰፋ የተተረጎመ

 መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አሥራ ሁለት ነገዶች ሲናገር፣ ስለ አንድ አካል ቤተክርስቲያን አይናገርም ለያይቶ ነው ያስቀመጣቸው  (ሮሜ 12፡5፣ ኤፌ 1፥22-23 እና 4፡4)።

 አሥራ ሁለት የእስራኤል ነገዶች



 የእስራኤል ብሔር የሆኑ አሥራ ሁለት ቤተሰብ ነገዶች ነበሩ።  እነዚያ ነገዶች ከአሥራ ሁለቱ የያዕቆብ ልጆች የመጡ ናቸው

 -(ዘፍ 49፡28)።

 እስራኤል ሕጉን ሁሉ ለማድረግ በተስማሙ ጊዜ፣ ሙሴ ለመታሰቢያ የሚሆን አሥራ ሁለት ሀውልቶች  ሠራ፤ ለእያንዳንዱ የእስራኤል ነገድ አንድ ም።

“ሙሴም የእግዚአብሔርን ቃሎች ጻፈ ማለዳም ተነሣ፥ ከተራራውም በታች መሠዊያን፥ አሥራ ሁለትም ሐውልቶች ለአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ሠራ።”

  — ዘጸአት 24፥4

 በአሮን ኤፉድ ውስጥ እንደ አሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ አሥራ ሁለት ድንጋዮች ነበሩ።

 “የዕንቈቹም ድንጋዮች እንደ እስራኤል ልጆች ስሞች አሥራ ሁለት ይሆናሉ፤ በየስማቸውም ማተሚያ እንደሚቀረጽ ይቀረጹ፤ ስለ አሥራ ሁለቱ ነገዶችም ይሁኑ።”

  — ዘጸአት 28፥21

መልካሙንም ዱቄት ወስደህ አሥራ ሁለት ኅብስት ጋግር በአንድ ኅብስት ውስጥ ከመስፈሪያው ከአሥር እጅ ሁለት እጅ ይሁን። እነዚህንም ስድስት ስድስቱን በሁለት ተርታ አድርገህ በእግዚአብሔር ፊት በጥሩ ገበታ ላይ አኑራቸው።ለእግዚአብሔርም ለእሳት ቍርባን በእንጀራው ላይ ለመታሰቢያ ይሆን ዘንድ በሁለቱ ተርታ ላይ ጥሩ ዕጣን አድርግ።በእግዚአብሔር ፊት ሁልጊዜ በሰንበት ቀን ሁሉ በተርታ ያድርገው፤ በእስራኤል ልጆች ዘንድ የዘላለም ቃል ኪዳን ነው።ለአሮንና ለልጆቹም ይሁን፤ በእሳት ከተደረገው ከእግዚአብሔር ቍርባን በዘላለም ሥርዓት ለእርሱ ቅዱሰ ቅዱሳን ነውና በተቀደሰ ስፍራ ይብሉት። 

 - ዘሌዋውያን 24፥5-9

 እስራኤል ወደ ተስፋይቱ ምድር ሲገቡ እግዚአብሔር ምድሪቱን እንዲሰልሉ አሥራ ሁለት ሰዎች ላከ፤ ከእያንዳንዱ ነገድ አንድ አለቃ ይህ በሙሴ የተደረገ ነው

  እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው ለእስራኤል ልጆች የምሰጣትን የከንዓንን ምድር ይሰልሉ ዘንድ ሰዎችን ላክ፤ ከአባቶች ነገድ ሁሉ እያንዳንዱ በመካከላቸው አለቃ የሆነ አንድ ሰው ትልካላችሁ።

  — ዘኍልቍ 13:2-3

 ከሙሴ ጋር ባይገቡም ኢያሱ በዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ ወደ ተስፋይቱ ምድር በገቡ ጊዜ ይህን የአሥራ ሁለት ሰዎች ምርጫ ደገመው እንደ ሙሴ 

“አሁንም ከእስራኤል ነገዶች አሥራ ሁለት ሰዎች ምረጡ፤ ከየነገዱ አንድ አንድ ሰው ይሁን።”

  — ኢያሱ 3፥12

እንዲህም ሆነ፤ ሕዝቡ ሁሉ ዮርዳኖስን ፈጽመው በተሻገሩ ጊዜ እግዚአብሔርም ኢያሱን፦

 ከሕዝቡ ከየነገዱ አንድ አንድ ሰው፥ አሥራ ሁለት ሰዎች ምረጥና፦

 -ኢያሱ 4፥1-2

“ከዮርዳኖስም ውስጥ የወሰዱአቸውን እነዚያን አሥራ ሁለቱን ድንጋዮች ኢያሱ በጌልገላ አቆማቸው።”                            

 — ኢያሱ 4፥20  

ለ እያንዳንዱ ነገድ ወንዙን በተሻገሩበት በጌልገላ አንድ ድንጋይ ተወ። ምድሪቱም ለአሥራ ሁለት ክፍሎች ተከፈለች፥ ለእያንዳንዱ ነገድ አንድ።

-ኢያሱ ምዕራፍ 13 እና 14 ይነበብ

 አሥራ ሁለት ነገዶች እና መሲሑ

 አሥራ ሁለቱ ነገዶች በኢየሱስ ምድራዊ አገልግሎት ውስጥ በሚገኙበት ጊዜም እንኳ እስራኤልን ሁልጊዜ ያመለክታሉ።

 የእስራኤል መሲህ ከእርሱ ጋር የሚያገለግሉትን አሥራ ሁለት ሰዎችን መረጠ፤ አንድ ለእስራኤል ነገድ ለእያንዳንዱ ነገድ  

  -(ማርቆስ 3፡14)።

 እነዚህን አሥራ ሁለቱ ሰዎች ወደ አሕዛብ እንዳይሄዱ ወደ አሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ብቻ እንዲሄዱ ትእዛዝ ሰጣቸው።

 “እነዚህን አሥራ ሁለቱን ኢየሱስ ላካቸውና አዘዛቸው፡- ወደ አሕዛብ መንገድ አትሂዱ ወደ ሳምራውያንም ከተማ አትግቡ፤ ይልቁንም ከእስራኤል ቤት ወደ ጠፉ በጎች ሂዱ።

 — ማቴዎስ 10:5-6

 ለእነዚህ አሥራ ሁለቱ ሐዋርያት በአሥራ ሁለት ዙፋን ላይ እንደሚቀመጡ ቃል ገባላቸው፤ ለእያንዳንዱ የእስራኤል ነገድ አንድ ዙፋን ይሆናል።

 “ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፡- እውነት እላችኋለሁ፥ እናንተ የተከተላችሁኝ በዳግመኛ ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ እናንተ ደግሞ በአሥራ ሁለቱ ነገድ ስትፈርዱ በአሥራ ሁለት ዙፋን ትቀመጣላችሁ።  እስራኤል።"       

— ማቴዎስ 19፥27-28

 አሥራ ሁለት ነገዶች እና መንግሥት

 አሥራ ሁለቱ ሐዋርያት መሲሑንና መንግሥቱን ለአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች አገልግለዋል።

 “የእስራኤል ሰዎች ሆይ፣ እነዚህን ቃሎች ስሙ…”

—የሐዋርያት ሥራ 2:22

 "የእግዚአብሔርና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ያዕቆብ ለተበተኑ ለአሥራ ሁለቱ ወገኖች፥ ሰላም ለእናንተ ይሁን።  

—ያዕቆብ 1:1

 በመጨረሻው ቀን ከእያንዳንዱ ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ አገልጋዮች ሆነው እንደሚታተሙ ዮሐንስ ተንብዮአል።

 " የታተሙትንም ቍጥር ሰማሁ፥ ከእስራኤልም ልጆች ነገድ ሁሉ የታተሙት መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ።  

— ራእይ 7:4

 በመንግሥቱ የምትመጣው አዲሲቷ ኢየሩሳሌም እንኳን አሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶችን የሚወክሉ በአሥራ ሁለት መሠረት ላይ አሥራ ሁለት በሮች አሏት። ታላቅና ረጅም ቅጥር ነበራት፥ አሥራ ሁለትም ደጆች ነበሯቸው በደጆቹም አሥራ ሁለት መላእክት ነበሯቸው፥ በላዩም የአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ልጆች ነገድ ስሞች ተጽፈውባቸው ነበር።

 አሥራ ሁለት ነገዶች የአካል ቤተ ክርስቲያን አይደሉም

 አንድ አካል ስለምትሆን ቤተ ክርስቲያን የሚናገረውን መጽሐፍ አሥራ ሁለት ነገዶች ካሉት ሕዝብ መከፋፈል ቀላል ነው።  የአንድ አካል ቤተ ክርስቲያን አሥራ ሁለት ነገድ የላትም።

 በመጽሐፍ ቅዱሳችሁ ውስጥ አሥራ ሁለቱ ነገዶች በሚገኙበት፣ በእስራኤል በኩል ስለሚሠራው እግዚአብሔር ስራ እየተናገረ ነው።  እግዚአብሔር የምድር ላይ አጀንዳ የሚሠራው በአሥራ ሁለቱ ነገድ ሲሆን የሰማይ አጀንዳ ደግሞ በቤተክርስቲያን በኩል  ብቻ ነው።

 ይህ ማለት አንድ አካል የሆነችው ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ከዘፍጥረት እስከ ሚልክያስ፣ ኢየሱስ ለእስራኤል ባደረገው ምድራዊ አገልግሎት፣ በበዓለ ሃምሳ በሐዋርያት ሥራ ወይም የራዕይን መጽሐፍ ጨምሮ በሐዋርያት በኩል ለአሥራ ሁለቱ ነገዶች በተጻፉት የዕብራይስጥ መልእክቶች ውስጥ የትም ስፍራ ላይ አትገኝም።

 እግዚአብሔር በእስራኤል በኩል በምድር ላይ ሲሰራ የነበረው ሰውነቱ አካሉ በሆነችው ቤተክርስቲያን በኩል እየሰራ አይደለም።

 እስራኤል የትንቢት ርዕሰ ጉዳይ ናት፣ አንዲት አካል ቤተክርስቲያን ደግሞ ለአስራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ያልተገለጠ የምስጢር ርዕሰ ጉዳይ ነች።

ፀጋ ከመንፈሳችሁ ጋር ይሁን 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ጸድቀናል (ታረቅን)

ኩነኔ የለብንም

እምነት መገኛው ቃሉ ነው