ልጥፎች

ከኖቬምበር, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የእስራኤል እና የክርስቶስ አካል ልዮነት

ምስል
 የክርስቶስ አካል የሆነችው ቤተ ክርስቲያን ከአይሁድና ከአሕዛብ የተዋቀረች አዲስ ፍጥረት እንጂ አሥራ ሁለት ነገድ የላትም።   ጀስቲን ጆንሰን እንደተየበው በ ይሳቅ አሰፋ የተተረጎመ  መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አሥራ ሁለት ነገዶች ሲናገር፣ ስለ አንድ አካል ቤተክርስቲያን አይናገርም ለያይቶ ነው ያስቀመጣቸው  (ሮሜ 12፡5፣ ኤፌ 1፥22-23 እና 4፡4)።  አሥራ ሁለት የእስራኤል ነገዶች  የእስራኤል ብሔር የሆኑ አሥራ ሁለት ቤተሰብ ነገዶች ነበሩ።  እነዚያ ነገዶች ከአሥራ ሁለቱ የያዕቆብ ልጆች የመጡ ናቸው  -(ዘፍ 49፡28)።  እስራኤል ሕጉን ሁሉ ለማድረግ በተስማሙ ጊዜ፣ ሙሴ ለመታሰቢያ የሚሆን አሥራ ሁለት ሀውልቶች  ሠራ፤ ለእያንዳንዱ የእስራኤል ነገድ አንድ ም። “ሙሴም የእግዚአብሔርን ቃሎች ጻፈ ማለዳም ተነሣ፥ ከተራራውም በታች መሠዊያን፥ አሥራ ሁለትም ሐውልቶች ለአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ሠራ።”   — ዘጸአት 24፥4  በአሮን ኤፉድ ውስጥ እንደ አሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ አሥራ ሁለት ድንጋዮች ነበሩ።  “የዕንቈቹም ድንጋዮች እንደ እስራኤል ልጆች ስሞች አሥራ ሁለት ይሆናሉ፤ በየስማቸውም ማተሚያ እንደሚቀረጽ ይቀረጹ፤ ስለ አሥራ ሁለቱ ነገዶችም ይሁኑ።”   — ዘጸአት 28፥21 መልካሙንም ዱቄት ወስደህ አሥራ ሁለት ኅብስት ጋግር በአንድ ኅብስት ውስጥ ከመስፈሪያው ከአሥር እጅ ሁለት እጅ ይሁን። እነዚህንም ስድስት ስድስቱን በሁለት ተርታ አድርገህ በእግዚአብሔር ፊት በጥሩ ገበታ ላይ አኑራቸው።ለእግዚአብሔርም ለእሳት ቍርባን በእንጀራው ላይ ለመታሰቢያ ይሆን ዘንድ በሁለቱ ተርታ ላይ ጥሩ ዕጣን አድርግ።በእግዚአብሔር ፊት ሁልጊዜ በሰንበት ቀን ሁሉ ...

ለኃጢአት ሞተናል

ምስል
 ሮሜ 6 ¹ እንግዲህ ምን እንላለን? ጸጋ እንዲበዛ በኃጢአት ጸንተን እንኑርን? አይደለም። ² ለኃጢአት የሞትን እኛ ወደ ፊት እንዴት አድርገን በእርሱ እንኖራለን? Romans 6 (KJV) ¹ What shall we say then? Shall we continue in sin, that grace may abound? ² God forbid. How shall we, that are dead to sin, live any longer therein? "ለኃጢአት የሞትን እኛ ወደ ፊት እንዴት በእርሱ እንኖራለን?" የሚለው ሐረግ የአጻጻፍ ጥያቄ ነው።  ጳውሎስ መልስ እየጠበቀ አይደለም ነገር ግን ክርስቶስን የተቀበሉ እና 'ለኃጢአት የሞቱ' ሰዎች በኃጢአት መኖራቸውን መቀጠል እንደሌለባቸው God forbid እግዚአብሔር ይሄንን ከልክሏል ይላል!!! ይህን በመግለጽ በሮም ላሉት አማኞች እውነቱን ለማጉላት አንድ ነጥብ እየተናገረ ነው።  እውነታው ግን ለኃጢአት የሞተ ሰው (በክርስቶስ ላይ ባለው እምነት) በኃጢአት ውስጥ መኖርን ለመቀጠል አቅም የለውም አቅም (ፀጋ) ያለው በፅድቅ ለመኖር ነው።  ለውጥ በአማኝ ሕይወት ውስጥ መከሰት አለበት፣ ከኃጢአተኛ ምግባራት እየራቁ እና በክርስቶስ ባለው አዲሱ ማንነታቸው እንደሚገባ እየኖሩ ለጌታ እንዲኑ ይመክራል። ዛሬም እኛ ይህም በራሳችን ጥንካሬ ልናደርገው የምንችለው ነገር አይደለም።  የእግዚአብሔር ሥራ ፀጋ ነው፣ በተጻፈ ቃሉ፣ የሚያጥበን እና አእምሮአችንን የሚያድስ፣ እና በህይወታችን፣ በንግግራችን፣ በሃሳባችን፣ በድርጊታችን እና በህይወታችን ምላሾች ላይ ተጽእኖ ማድረግ ይጀምራል።  ለሥጋዊ ተፈጥሮአችን መሞትን እንድንጀምር እና የክርስቶስን ባሕርይ እንድንለብስ የሚያደርገን የተጻፈ ቃል ነው። ፀጋ ይብዛላችሁ ?...

እግዚአብሔር ከአንተ የሚፈልገው አንድ ነገር ብቻ ነው

ምስል
 አንዴ ከዳንክ እግዚአብሔር ከአንተ የሚፈልገው አንድ ነገር ብቻ ነው።  እውነትን ወደ ማወቅ እንድትመጣ ይፈልጋል!  እግዚአብሔር ቃሉን እንድትማር ይፈልጋል።  ቃሉ እንዲሞላህ፣ እንዲያጠግብህ፣ ተጽዕኖ እንዲያሳድርብህ እና ከአንተ እንዲወጣ ይፈልጋል።  በቃሉ እውቀት ከኖርክ፣ እና ሀሳብህ፣ ንግግርህ፣ ድርጊትህ እና ምላሽህ፣ እና ውሳኔዎችህ በቃሉ ተጽእኖ ስር ከሆኑ እና በቃሉ መሰረት፣ በመንፈስ እየተመላለስክ ነው።  ኢየሱስም _“ቃሌ መንፈስ ነው ሕይወትም ነው” ብሏል።_ የእግዚአብሔር ቃል የሕይወትህ ሁሉ ምንጭ ሲሆን በመንፈስ ትመላለሳለህ። በቃሉ እውቀት እየተነካ ነው።  የእግዚአብሔርን ቃል ባወቅህ መጠን ፈቃዱንና መንገዶቹን በይበልጥ ባወቅህ መጠን እና የበለጠ ስትረዳ በመንገዱ ውስጥ ትሄዳለህ።  ይህ ሲሆን የሥጋን ሥራ መናቅ ትጀምራለህ። “እንደ ሥጋ ፈቃድ ብትኖሩ ትሞቱ ዘንድ አላችሁና፤ በመንፈስ ግን የሰውነትን ሥራ ብትገድሉ በሕይወት ትኖራላችሁ።”    ሮሜ 8፥13 “ነገር ግን እላለሁ፥ በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ።”    ገላትያ 5፥16 ቃሉ ከአንተ በወጣ ቁጥር የክርስቶስ ህይወት ከህይወትህ ላይ ይፈሳል።  ኃጢአትን ማሸነፍ የሚቻለው በዚህ መንገድ ነው።  ሥጋን ማሸነፍ የሚቻለው በዚህ መንገድ ነው።  ህግን በማዘጋጀት አይደለም.  በዲሲፕሊን አይደለም። በራስ ፈቃድ እና በሰዎች ጥንካሬ አይደለም። ይህ ሁሉ ይከሽፋል እና ዞሮ ይኮንናል እናም በአንተ ውስጥ ላለው የመንፈስ አሠራር ሞትን ያመጣል  ፊደል ይገድላል መንፈስ ግን ሕይወትን ይሰጣል።  ስለዚህ አሁንም እላለሁ እግዚአብሔር ከአንተ ምን ይፈ...